መላክ እንዴት ይሠራል
ትዕዛዝ ከፈጠሩበት ጊዜ ጀምሮ ዕቃው የተቀባዩ እጅ እስኪገባ ድረስ።
የሚልኩ ከሆነ
ትዕዛዙን ይፍጠሩ
በመተግበሪያው ዕቃውን ይግለጹ፣ የሚረከብበትን ቦታ ይምረጡ፣ የተቀባዩን ስም እና ስልክ ቁጥር ያስገቡ።
ዋጋውን አይተው ያረጋግጡ
ከማረጋገጥዎ በፊት መተግበሪያው ሙሉ ዋጋውን ያሳያል። እስኪያረጋግጡ ድረስ ምንም አይከፈልም።
በመረከቢያ ኮድዎ ያስረክቡ
አሽከርካሪው ዕቃውን አይቶ የመረከቢያ ኮድዎን ያስገባል። ከዚያ በኋላ ብቻ ጉዞ ይጀምራል።
የሚቀበሉ ከሆነ
ኤስኤምኤስ ይደርስዎታል
ማን ምን እንደሚልክልዎ ይነግርዎታል፤ ትዕዛዙን የሚከታተሉበት ሊንክም አለው። መተግበሪያው አያስፈልግዎትም።
ከተጠየቁ ምላሽ ይስጡ
የማድረሻ ክፍያውን የሚከፍሉት እርስዎ ከሆኑ ሊንኩን ይክፈቱ፣ ወደ ስልክዎ በምንልከው ኮድ ያረጋግጡ፣ ከዚያም ይቀበሉ ወይም ውድቅ ያድርጉ።
በማስረከቢያ ኮድዎ ይረከቡ
አሽከርካሪው ሲደርስ መጀመሪያ ዕቃውን ያረጋግጡ። ከዚያ የማስረከቢያ ኮድዎን ይስጡ።
ማን ይከፍላል
አብዛኛውን ጊዜ ላኪው በመተግበሪያው በሞባይል ገንዘብ ይከፍላል። ላኪው ተቀባዩ እንዲከፍል መጠየቅም ይችላል። በዚህ ጊዜ ተቀባዩ መጀመሪያ ይቀበላል፤ ከዚያም በኦንላይን ወይም አገልግሎቱ ባለበት ቦታ ዕቃው ሲደርስ ለአሽከርካሪው በጥሬ ገንዘብ ይከፍላል።
በእያንዳንዱ ርክክብ ደኅንነት
የመረከቢያ ኮድ
ለላኪው በመተግበሪያው ይታያል። አሽከርካሪው ዕቃውን ለመረከብ ያስፈልገዋል።
የማስረከቢያ ኮድ
ዕቃው ከተረከበ በኋላ ለተቀባዩ በኤስኤምኤስ ይላካል። ዕቃውን ከተቀበሉ በኋላ ብቻ ለአሽከርካሪው ይስጡ።
መላክ የማይፈቀዱ ነገሮች
ሕገ ወጥ፣ አደገኛ ወይም የተከለከሉ ዕቃዎች ተቀባይነት የላቸውም። መተግበሪያው መላክ የሚችሏቸውን ዓይነቶች ያሳያል፤ አሽከርካሪውም ሲረከብ ዕቃውን ይፈትሻል።
ችግር ቢፈጠር
ተቀባዩ ካልተገኘ
አሽከርካሪው ተቀባዩን ለማግኘት ይሞክራል፤ ይጠብቃልም። አሁንም ማድረስ ካልተቻለ ቡድናችን እንደገና ይሞከር ወይም ዕቃው ይመለስ እንደሆነ ይወስናል።
መመለስ
የሚመለስ ዕቃ ወደተረከበበት ቦታ ይመለሳል። ላኪው ለአሽከርካሪው የሚሰጠው የመመለሻ ኮድ ይደርሰዋል።
ችግርን ማሳወቅ
ላኪዎች ችግርን ከመተግበሪያው ያሳውቃሉ። ተቀባዮች ያልፈለጉትን ጥያቄ ጨምሮ ከትዕዛዙ ሊንክ ማሳወቅ ይችላሉ።